
ባሕር ዳር: ሰኔ 02/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ግብርና ሚኒስቴር አሁናዊ ሀገራዊ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭትን በተመለከተ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም በቀጣይ 20 ቀናት ወይንም እስከ ሰኔ 21/2015 ዓ.ም ተጠናቆ ጅቡቲ ወደብ ይገባል ብሏል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ.ር) በሰጡት መግለጫ እ.አ.አ ሰኔ 11፣ 18፣ 25 እና 28/2023 አራት መርከቦች ማዳበሪያውን ያጓጉዛሉ ብለዋል።
ግዢ ከተፈጸመበት 12 ነጥብ 87 ሚሊዮን ኩንታል ውስጥ 6 ነጥብ 25 ሚሊዮን ያህሉ ወደ ሀገር ውስጥ ግብቷል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ወደ አርሶ አደሩ ተሰራጭቷል ነው ያሉት፡፡ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ደግሞ በተለያዩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት መካዝኖች ስለመኖሩም አንስተዋል።
ሚኒስትር ዴኤታዋ የአቅርቦት ክፍተቶች ቢስተዋሉም ቀድመው ለሚዘሩ ሰብሎች ቅድሚያ ሰጥቶ የማሰራጨትና በፍጥነት ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ችግር እንዳለም አንስተዋል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!