ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ተወያዩ ።

95

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። አይኤስ አይኤስ የሽብር ቡድንን ለማጥፋት የተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ስብስባ ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ተካሄዷል።

በስብስባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተሳተፉ ሲሆን ከስብሰባው ጎን ለጎን ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጋር ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ ሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ፣ በሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ስላለው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የሽግግር ፍትሕ ሂደት፣የሰብአዊ መብቶች እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከሳሽ ሲሽኮረመም ተከሳሽ ይኾናል” ረዳት ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ
Next articleበምሥራቅ አማራ የተከሰተውን የተምች ወረርሽኝ ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ መኾኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡