
ባሕር ዳር : ሰኔ 1/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አሜሪካ በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል ተጨማሪ የ112 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አድርጋለች፡፡
ድጋፉ በአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች የአስቸኳይ ጊዜ የኤች አይ ቪ ኤድስ ማገገሚያ ዕቅድ ፕሮግራም (ፔፕፋር) በኩል የሚተገበር ሲሆን ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2030 ኤች አይ ቪን ለማጥፋት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል መሆኑ ታውቋል።
የተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ በደማቸው ውስጥ ኤች አይ ቪ ለሚገኝ ዜጎች የሚደረገውን እንክብካቤ ለማጠናከር እና በ2030 ኤች. አይ .ቪ ኤድስን ከኅብረተሰብ ጤና ስጋትነት እንዲወጣ ለማድረግ ያግዛል ተብሏል፡፡
አሜሪካ በዚህ ፕሮግራም በኩል ባለፉት 20 ዓመታት በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚውል 3 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን የአሜሪካን ኤምባሲ ጠቅሶ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!