
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 01/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሳዑዲ እየተካሄደ ባለው አይ ኤስ አይ ኤስ የሽብር ቡድንን ለመዋጋት በተቋቋመው ዓለም አቀፍ ጥምረት የሚኒስትሮች ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው።
በጉባዔው የተለያዩ ሀገራት ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ሲሆን፤ ሚኒስትሮች የሽብር ቡድኑን በሁሉም ግንባሮች ለመዋጋት ያላቸውን ቁርጠኝነት ይገልጻሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አቶ ደመቀ መኮንን ከጉባዔው ጎን ለጎን የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!