ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን ድል ቀናቸው፡፡

99

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በስዊድን ስቶክሆልም ማራቶን ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ከአንድ እስከ ሦስት ያለውን ደረጃ በመያዝ በበላይነት አጠናቀዋል።

በወንዶች አትሌት አሸናፊ ሞገስ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ አትሌት ደራራ ሁሬሳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ጸጋዬ መኮንን ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው በመግባት ውድድሩን በበላይነት ጨርሰዋል።

በሴቶቹ ውድድር አትሌት ሲፈን መላኩ አንደኛ፣ አትሌት ሶሮሜ ነጋሽ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት የኔነሽ ዲንቄሳ ሦስተኛ በመሆን አሸንፈዋል።

በስፔን አልባሴቴ የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ካሳነሽ ባዜ ስታሸንፍ በደቡብ አፍሪካ በተደረገው የኔልሰን ማንዴላ ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት በቀለች ወሬዮ ሦስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

አትሌት ሰላም ገብሬ እና ትዕግሥት አያሌው በቅደም ተከተል አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተማሪዎችንና የመምህራንን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ የሙያ ትምህርት መለማመጃ ማዕከላት በትምህርት ቤቶች እንዲጠናከሩ ተጠየቀ፡፡
Next articleየአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭት ፈጣን፣ ፍትሐዊ እና ከሕገ ወጦች የጸዳ እንዲኾን እየሠራ መኾኑን ገለጸ።