“ለነጻነታችን ዋጋ ከፍለንበታል ወደ ኃላ ላንመለስ ነጻ ወጥተናል” የወልቃይት ወረዳ ነዋሪዎች

174

ሁመራ፡ ግንቦት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ነዋሪዎች መንግሥት የማንነታቸውን ጥያቄ በሕግ እንዲያጸድቅላቸውና የበጀት ተጠቃሚ እንዲኾኑ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።

ሕዝባዊ ሰልፉ በሁመራ ፣ በዳንሻ ፣ በማይካድራ ፣ በወልቃይት ፣ በጠገዴ ፣በአደባይ ፣ በብዓከር እና በሌሎች ከተሞች ተካሂዷል።

የወልቃይት ወረዳ ነዋሪዎችም ለነጻነታችን ዋጋ ከፍለንበታል ወደ ኃላ ላንመለስ ነጻ ወጥተናል ብለዋል።

ነጻነታቸውን ለማግኘት ደምና አጥንታችንን ገብረናል ፣ አማራዊ ማንነታችንን ለመንጠቅ የዘር ማጥፋት ወንጀልና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞብናል፤ ባሕልና ወጋችንን ለማጥፋት የማንነት ጭፍለቃ ደርሶብናል ብለዋል።

በመኾኑም መንግሥት አሁን ያገኘነውን ነጻነትና ሰላም እውቅና ሊሰጠንና ሊያረጋግጥልን ይገባል።
የማይገባንን አልፈለግንም አልጠየቅንም፤ የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም ብለዋል።

በሕዝባዊ ሰልፉም :-

✍️ለእንግዶች እንጅ ለወንጀለኞች ቦታ የለንም
✍️ተበዳይ እንጅ በዳይ ፣ተጨፍጫፊ እንጅ ጨፍጫፊ ፣ ተወራሪ እንጅ ወራሪ ፣ ተፈናቃይ እንጅ አፈናቃይ አይደለንም
✍️አማራዊ ማንነታችን የወሰን አስተዳደር ግዛታችን በሕግ አግባብ ይከበር
✍️ወልቃይት ጠገዴ የአማራ የዘር ግንድ መነሻ ነው
✍️ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ነው

የሚሉ ድምጾችን አሰምተዋል።
ሕዝባዊ ሰልፉ በደማቅ ኹኔታ ተከናውኗል።

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምሥራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ 36 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የጠጠር መንገድ በኀብረተብ ተሳትፎ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።
Next article“የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከፍ ሲል ኢትዮጵያዊ ዝቅ ሲል አማራ ነዉ” ኮኔሬል ደመቀ ዘዉዱ