ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያዩ፡፡

205

ፕሬዝዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያዩ፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ውይይቱን ያካሄዱት በኪጋሊ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም አቀፉ የሥርዓተ ፆታ ጉባኤ ጎን ለጎን ነው።

የሁለቱን ሀገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ የሐሳብ ልውውጥ ማድረጋቸውም ተገልጿል።

ዛሬ ረፋድ ደግሞ በጽሕፈት ቤታቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመጠለያ ጉዳዮች ድርጅት ኃላፊ ማይሙና ሞድን አነጋግረዋል:: ድርጅቱ በኢትዮጵያ እየሠራ ስላለው ሥራም በዝርዝር ተነጋግረዋል::

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት

Previous articleበውጭ ሀገራት የሚኖሩ አማራዎች በተቀናጀ መልኩ ለክልሉ ልማትና ሰላም እንዲሰሩ የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጥሪ አቀረቡ።
Next articleየአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በውሕድ ፓርቲው እንደሚመለሱ የአዴፓ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ገለጹ፡፡