
ሁመራ፡ ግንቦት 27/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሰላማዊ ሰልፉ የማንነት ጥያቄዎች እና የበጀት ጉዳይን በዋናነት መሰረት ያደረገ ነው።
በሰላማዊ ሰልፉ የዞኑ ሕዝብ ለሶስት አስርት ዓመታት ማንነቱ ሳይከበር የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲደርስበት መቆየቱን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል ።
ከሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ በተደረገው መራር ትግል ነጻነታችንን አስመልሰናል የሚሉት ነዋሪዎቹ አሁን ላይ የማንነት እና የበጀት ጥያቄያቸው በሕጋዊ መንገድ እንዲፈታ ጠይቀዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ የተለያዩ መልዕክቶች ተላልፈዋል ።
ከነዚህ መካከል:-
👉የወልቃይት እና የአማራ ማንነት ጥያቄን የርስት ማስመለስ ብሎ በመፈረጅ አማራን ማሸማቀቅ አይቻልም! ሀገር ርስት ነው። ለርስት መሞት ክብር ነው
👉የማይገባንን አልፈን አልጠየቅንም፣ የራሳችንንም አሳልፈን አንሰጥም
👉የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ጥምር ጦሩ የከፈለውን መስዋዕትነት እናከብራለን ፣እንዘክራለን ፣ድሉንም እናስቀጥላለን
👉የአማራን ሕዝብ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት መነጠል አይቻልም፣ መከላከያ የሕዝባችን አቅም፣ የሕዝባችን የመከላከያ ምንጭ ነው የሚሉት ይገኙበታል።
ዘጋቢ፦ አዲስ ዓለማየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!