አማራ ባንክ አዲስ የዲጂታል መተግቢያ ለማስጀመር የውል ስምምነት ተፈራረመ።

120

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ባንክ ለደንበኞቹ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና ከጥሬ ገንዘብ ግብይት በቀላለ መልኩ ባሉበት ቦታ መገልገል እንዲችሉ የዲጂታል ሥራዎችንና አገልግሎቶችን ለማስፋት እየሠራ ይገኛል።

በንግድ ተቋማት ውስጥ ያሉ ኪው አር (QR) ኮድን በመጠቀም በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ በማንበብ ስካን በማድረግ ክፍያ መፈፀም እንዲችሉም ዛሬ “ሳንቲም ፔይ” ከተሰኘ ተቋም ጋር የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።

በዚህ የክፍያ ሥርዓት አገልግሎት ሰጭዎች የተለየ ቴክኖሎጂ ማስገጠም ሳይጠበቅባቸው በአማራ ባንክ ሂሳባቸው “ሳንቲም ፔይ ኪው አር (QR)” ተዘጋጅቶላቸው መከወን ይችላሉ ተብሏል።

አገልግሎት ሰጭዎች ከደንበኞች ጋር ይህንን ለማድረግ “የሳንቲም ፔይ” አጋርነት ስምምነት የሚያስፈልጋቸው ሲኾን በዚህም ተጠቃሚው ወደ አገልግሎት ሰጭው በቀጥታ ክፍያ መፈፀም ይችላል ተብሏል።

በባንኩ የዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ኀላፊ በፍቃዱ ቸርነት አማራ ባንክ የዲጂታል ግልጋሎቱን በስፋት እየዘረጋ መኾኑን አንስተዋል። “ጉዞ ጎ” ን በመጠቀም የአየር መንገድ ትኬት መቁረጥ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲኾን የ “ዩ ኤስ ኤስ ዲ” የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ደግሞ ባሉበት ቦታ ኾነው ከአማራ ባንክ ወደ ሌሎች ባንኮች ሂሳብ ማንቀሳቀስ ይችላሉ ተብሏል።

ይህ “ከሳንቲም ፔይ” ጋር የተደረገው ስምምነትም ለደንበኞች ቀልጣፋ ግልጋሎት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል አቶ በፍቃዱ።

“የሳንቲም ፔይ” ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ትንሳዔ ደሳለኝ “ከአማራ ባንክ ጋር ያደረጉት ስምምነት ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ እንዲሆኾን እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበመካነ ሰላም ከተማ የተከሰተ ድንገተኛ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የከተማዋ ፖሊስ ገለጸ።
Next articleተጠባቂው የማንቼስተር ደርቢ