
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የመካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ጽሕፈት ቤት የወንጀል ታክቲክ ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ክንዱ ወርቅነህ እንደገለፁት፤ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም በመካነ ሰላም ከተማ ቀበሌ ሁለት ህዳሴ ሆቴል አካባቢ በግምት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
በተከሰተው ድንገተኛ የእሳት አደጋ በሁለት ጋራጅ ቤቶች፣ በአምስት ሱቆች ላይ እንዲሁም በመብራት ኀይል ገመዶችና በቴሌ ገመዶች ላይ ጉዳት መድረሱን ልጸዋል።
የወደመውን የንብረት መጠንና የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን የገለፁት ረ/ኢንስፔክተር ክንዱ ወርቅነህ አደጋው ተባብሶ ወደ ሌሎች አካባቢ እንዳይዛመት በፀጥታ ኀይሉና በኅብረተሰቡ ትብብር አደጋው መቆጣጠር መቻሉን ገልፀዋል። መረጃው የመካነ ሰላም ከተማ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!