
ባሕር ዳር: ግንቦት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 14ኛው ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ሳምንት ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ግዮን ሆቴል ተከፍቷል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኀላፊ ሰርፀ ፍሬ ስብሀት አዲስ አበባ ላይ በኪነጥበብ ዘርፉ በስፋት መሥራት ይገባል ብለዋል።
በርካታ የኪነጥበብ ሙያተኞችን ያፈራችው እና የዲፕሎማት ከተማዋ አዲስ አበባ በኪነ ጥበብ ዘርፉም የጎብኝዎች መዳረሻ እንድትኾን መሠራት አለበት ተብሏል።
ምክትል ቢሮ ኀላፊው አዲስ አበባ ከዓለም አቀፍ መድረኮችና ከታላላቅ ፌስቲቫሎች ልምዶችን መቅሰም እንዳለባት አንስተዋል። የኪነ ጥበብ ዘርፉም ልዩ ኢንቨስትመንት ይጠይቃል ነው ያሉት። በዚህ ፌስቲቫልም በርካታ የኪነጥበብ ሥራዎች ይተዋወቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸዉ አባቡ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!