
ባሕር ዳር : ግንቦት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በበጎ ፈቃድ ደም የሚለግሱ ሰዎችን ቁጥር በማሳደግ በደም እጥረት ሳቢያ እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረህዋስ ባንክ አገልግሎት ገለጸ፡፡
“ደም ይለግሱ ህይወት ያጋሩ ዘወትር ያጋሩ” በሚል መሪ ሀሳብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡
የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት በተለያዩ ምክንያቶች ደም የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ ነው፡፡
በአንጻሩ ግን የደም ለጋሾችን ቁጥር ከፍ ማድረግ ላይ አሁንም ክፍተቶች እንዳሉ ተናግረዋል።
በዚህም ይህንን ችግር ለመቅረፍ ግንዛቤን በማስፋት የደም ለጋሾችን ቁጥር ለማሳደግ ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
ደም መለገስ የሚችል ማንኛውም ሰው የሰዎችን ህይወት ለመታደግ የቻለውን እንዲያደርግም አቶ ሀብታሙ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች፣በተለገሱት ደም ሳቢያ በህይወት የቆዩ ተለጋሾች እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ሲል የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!