
ባሕር ዳር : ግንቦት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሥራ ፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች፣ ማሰልጠን፣ ማወዳደርና መሸልም ዓላማው ያደረገው ብሩህ ተስፋ 2015 ውድድር ከግንቦት 28 ጀምሮ ለ15 ቀናት በቡራዩ ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ማእከል እንደሚካሄድ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ በ2013 ዓ.ም የተጀመረው ብሩህ ተስፋ የሥራ ፈጠራ ውድድር አራተኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።
ውድድሩ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸውን ወጣቶች በየደረጃው በማወዳዳር ሀሳባቸው የሥራ ዕድል እንዲፍጥር የማድረግ ዓላማ ያለው ነው ብለዋል።
በዘንድሮው የውድድር በአንድ ሺ 240 ያህል ወረዳዎች፣ በ98 ዞኖች፣ በ50 ዪኒቨርስቲዎች የውድድር ማኑዋል ተዘጋጅቶ ተሰጥቶ። በዚህም ከአፋርና ደቡብ ም ዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች ውጪ በ10 ክልሎች በየደረጃው ውድድር እንዲካሄድ ተደርጓል።
በዚህ ዓመት 200 ሀስቦች በተለያዩ ደረጃዎች ቀርበው የሚወዳደሩ ሲሆን ከእነዚህም 70 የሚሆኑት ሀሳቦች ተለይተው በዳኞች አማካኝነት የመጨረሻዎቹን 50 ምርጥ ሀስቦች የሥራ መነሻ ካፒታል ለእያንዳንዳቸው አምስት ሺ ዶላር ሽልማት ይበረከትላቸዋል ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በመግለጫቸው፣ እስካሁን በተካሄዱ ሰባት ሀገር አቀፍና ክልላዊ ውድድሮች ሁለት ሺ 412 አመልካቾች ተሳትፈው ለ400 ሀሳብ ባለቤቶች ወይም 542 ወጣቶች የቡት ካምፕ ስልጠና ተሰጥቷል።
ለ167 ምርጥ ሀሳቦች የአንድ ሚሊዮን 518 ሺ ዶላር የመነሻ ሀሳብ ካፒታል ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ብለዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!