
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ከዳንግላ እስከ ግልገል በለስ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ድረስ መልሶ የተገነባው የ66 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
መስመሩ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጠ፣ ምሰሶዎቹ ያረጁና የዘመሙ በመሆኑ በተደጋጋሚ ጊዜ የሀይል መቆራረጥ ችግር ሲፈጠር ቆይቷል፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍ 140 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመልሶ ግንባታ ስራ የተከናወነ ሲሆን ከ650 በላይ ምሰሶዎች ተተክለዋል፡፡
የተከናወነው የመልሶ ግንባታ በአካባቢው የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ለመቀነስና አገልግሎቱን አስተማማኝ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
መስመሩ ፓዊ፣ ቻግኒ፣ ግልገል በለስ፣ ማንኩሽ፣ ድባጢ እና ዚገም ከተሞችን የኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን በተጠቀሱት ከተሞች ያሉትን ሌሎች ሳተላይቶችንም ተደራሽ ያደርጋል፡፡ መረጃው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!