የግብርና ኤግዚቢሽኑ 50 ሺህ ጎብኚዎችን አስተናግዷል።

47

ባሕር ዳር : ግንቦት 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሃሳብ ከአራት ሳምንት በፊት በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የግብርና ኤግዚቢሽን 50 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎብኘታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ እንደገለጹት፤ ኤግዚቢሽኑ ከተጀመረ አራት ሳምንታት የሆነው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ 50 ሺህ ጎብኚዎችን አስተናግዷል።
አግዚቢሽኑ ግንቦት 27 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ እንደሚጠናቀቅ ሚኒስትሩ አስታውቀው፤ በቀጣይ ቀናት ተጨማሪ ጎብኚዎች እንደሚኖሩ ገልጸዋል።

ኤግዚቢሽኑን አርሶ አደሮች፣ የልማት ሰራተኞች፤ ዓለም አቀፍ ተቋማት፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ህጻናት፣ የንግድ ማኅበረሰብ አባላትና ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ጨምሮ በርካታ ዜጎች እንደጎበኙት አመላክተዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ግብርና የሁሉንም ማኅበረሰብ ክፍል የሚመለከት ጉዳይ በመሆኑ ዜጎች ኤግዚቢሽኑን እንዲጎበኙ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የተሳካ ኤግዚቢሽን በመካሄድ ላይ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ኢፕድ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
Next articleከዳንግላ እስከ ግልገል በለስ የተገነባው ከፍተኛ መስመር አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ።