
ባሕር ዳር: ግንቦት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ቀን ሁለት ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋሉ።
በመርሐ-ግብሩ ሲዳማ ቡና ከአርባ ምንጭ ከተማ ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
በደረጃ ሰንጠረዡ ሲዳማ ቡና በ34 ነጥብ 10ኛ ደረጃን የያዘ ሲሆን አርባ ምንጭ ከተማ በ29 ነጥብ 14ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛል።
ሲዳማ ቡና በሊጉ ባደረጋቸው ያለፉት አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች አራቱን ሲያሸንፍ በአንዱ አቻ ወጥቷል።
ተጋጣሚው አርባ ምንጭ ከተማ በአንጻሩ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ሲያሸንፍ በአራቱ ነጥብ ተጋርቷል።
ጨዋታው ሲዳማ ቡና ከወራጅ ቀጠና ስጋት ለመራቅ እንዲሁም አርባ ምንጭ ከተማ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት የሚያደርጉት ጨዋታ መሆኑ ተጠባቂ ያደርገዋል።
ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያ ዙር ያደረጉት ጨዋታ ሶስት እኩል በሆነ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል።
በሌላኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ -ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከለገጣፎ ለገዳዲ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በደረጃ ሰንጠረዡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ55 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ የተቀመጠ ሲሆን ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ለገጣፎ ለገዳዲ በ15 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዟል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!