የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኀላፊዎች የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ።

52

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 24/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎበኙ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ፣ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች አውደ ርዕዩን ጎብኝተዋል።

አመራሮቹ ከጉብኝቱ ጎን ለጎንም በሲዳማ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች የተዘጋጀውና በሌማት ትሩፋት የተገኙ ውጤቶችን የሚያስቃኝ አውደ ርዕይን በሳይንስ ሙዚየም መርቀው ከፍተዋል።

በሁለቱ ክልሎች የተዘጋጀው አውደ ርዕይ ላይ የዓሳ ፣ ማር፤ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ውጤቶች ቀርበዋል።

”ከቤተ ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ላለፉት ሶስት ሳምንታት በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።

አውደ ርዕዩን የግብርና ሚኒስቴር፣ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት እና ኢትዮ- ቴሌኮም በጋራ አዘጋጅተውታል።

በአውደ ርዕዩ በኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ ያለበትን ደረጃ የሚያሳዩ ምርቶች፣ የግብርና ቴኖክሎጂዎች እና የምርምር ውጤቶች ለጎብኝዎች ከፍት ሆነዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፈር ማዳበሪያ እጥረት ግን አለ?
Next articleፀደይ ባንክ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለን አምባሳደር አድርጎ ሾመ።