የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ማስተካከያ ተደረገ

64

ባሕር ዳር: ግንቦት 23/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር እና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ በ27ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ የሰዓት ማስተካከያ ማድረጉን አስታውቋል።

የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም መደረግ ይጀምራሉ።

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ በሃዋሳ ከተማ አመሻሽ ላይ እየጣለ በሚገኘው ዝናብ ምክንያት የ27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚጀምሩበት ሰዓት ላይ ማስተካከያ ማድረጉን ገልጿል።

በዚሁ መሰረት በ9 ሰዓት እንዲጀምሩ ፕሮግራም የወጣላቸው ጨዋታዎች በሙሉ 7 ሰዓት እንዲሁም በ12 ሰዓት ይጀምሩ የነበሩ ጨዋታዎች ደግሞ 10 ሰዓት ላይ እንደሚጀመሩ አመልክቷል።

በተጨማሪም ጨዋታው ተጀምሮ በዝናብ ምክንያት የተቋረጠ ጨዋታ ካለ ጨዋታው በማግስቱ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በሃዋሳ አርተፊሻል ሜዳ ላይ እንዲጠናቀቅ ኮሚቴው ውሳኔ አስተላልፏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አቶ ደመቀ በቻይና የነበራቸው ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የኢንቨስትመንት እና የባሕል ግንኙነት ያሳደገ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Next articleበክልሉ በሚደረገው መልሶ ማቋቋምና ግንባታ በውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ፡፡