የ2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የማጣርያ ጨዋታዎች ድልድል ወጥቷል።

75

ባሕርዳር : ግንቦት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በመጀመርያው ዙር ከቻድ ጋር ስትደለደል የሁለቱ ሀገራት አሸናፊ በሁለተኛ ዙር ማጣርያ ከናይጄርያ ጋር የሚጫወት ይኾናል።

አራት ዙሮች ባሉት ማጣርያ የአንደኛ ዙር ማጣርያ ጨዋታዎች ከሐምሌ 3 እሰከ 11/2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ይደረጋሉ።

2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የማጣርያ ጨዋታዎች እጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ግብጽ ካይሮ ላይ መካሄዱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article11ኛው የአማራ ክልል የመስሪያ ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር በደሴ ከተማ ሊካሄድ ነው።
Next article“አቶ ደመቀ በቻይና የነበራቸው ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የኢንቨስትመንት እና የባሕል ግንኙነት ያሳደገ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር