
ባሕርዳር : ግንቦት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) 11ኛው የአማራ ክልል የመንግሥት ሰራተኞች ስፖርታዊ ውድድር ከግንቦት 27/2015 ዓ.ም እስከ ሰኔ 07/2015 ዓ.ም ድረስ በደሴ ከተማ እንደሚካሄድ የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል።
በወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የውድድር እና ተሳትፎ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምትኩ አክሊሉ ለብዙኃን መገናኛ ተቋማት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ውድድሩን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል ።
የውድድሩ ዓላማ የመንግሥት ሰራተኛው በማያቋርጥ አካላዊ እንቅስቃሴ እና ስፖርታዊ ውድድር ጤናውን መጠበቅ እና ምርታማነትን ማሳደግ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በአካልና በአእምሮው የበለጸገ ዜጋ እንዲኖር ለማስቻል ውድድሩ ያግዛል ብለዋል። ውድድሩ በሰራተኛው መካከል የውድድር መንፈስን በማሳደግ የአሸናፊነትን ስሜት እንደሚያሳድግ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!