በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጅ ባለሀብቶች በክልሉ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን ገለጹ።

270

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጅ ባለሀብቶች በክልሉ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን ገለጹ።

የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ዛሬ ማምሻውን በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ከሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጅ ባለሀብቶች ጋር በክልሉ ኢንቨስትመንት ጉዳይ መክረዋል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዮሀንስ ቧያለው እና የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ፈንታ ለባለሀብቶቹ ሥለ ክልሉ የልማት አቅም ማብራሪያ ሰጥተዋል። በአማራ ክልል በልማት እንዲሰማሩም ጥሪ አቅርበውላቸዋል። የቀረበውን ማብራሪያ መሠረት በማድረግም ባለሀብቶቹ እና የሥራ ኃላፊዎቹ ምክክር አድርገዋል።

ባለሀብቶቹ በተለይ ለአብመድ በሰጡት አስተያዬት በአማራ ክልል በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። የሥራ ኃላፊዎች ስለ ክልሉ ልማት ስላወያዩዋቸውም ባለሀብቶቹ አመሥግነዋል።

በአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በመሳተፍ ከራሳቸው አልፎ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ዝግጁ እንደሆኑም ነው የተናገሩት።

ዘጋቢ፦ አስማማው በቀለ- ከዋሽንግተን ዲሲ

Previous articleአዴኃን ከሌሎች የአማራን ሕዝብ ጥቅም ለማስከበር ከሚታገሉ ፓርቲዎች ጋር ያለውን ተቀራርቦ የመሥራት ጅማሮ እንዲያጠናክር ተጠየቀ፡፡
Next articleበክልሉ ከ4 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር በላይ ግብር ተሰብስቧል፡፡