የብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።

219

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ ግርማ የሺጥላ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።

ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ለውይይት በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላውን ሕዝብ በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ እንደሚመክር ከፓርቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለዘንድሮው የዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና በቂ ዝግጅት እያደረኩ ነው ” ትምህርት ሚኒስቴር
Next article“መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ቢደረጉም ዋጋቸው ቀንሶ ወደ ማኅበረሰቡ መድረስ አልቻሉም” የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር