“ምንጊዜም በላቀ የሥራ አፈጻጸም፣በላቀ ወታደራዊ ዲስፕሊን ሀገርና ሕዝባችሁን እንደምታገለግሉ እንተማመናለን” ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን

109

👉ከቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል ወደ አማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በፍላጎታቸው የተዘዋወሩ እና ሥልጠና ሲወስዱ የቆዩ አባላት የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

ደብረ ታቦር ፡ ግንቦት 20/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በቅርቡ በተሰራው የልዩ ኃይል ፖሊስ አባላትን መልሶ የማደራጀት ሥራ መሰረት ወደ አማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የተቀላቀሉ የቀድሞው የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በዓለም በር ፖሊስ ማሰልጠኛ ጣቢያ ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ዛሬ የምረቃ ሥነሥርዓቱ ተከናውኗል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው፣ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደጀኔ ልመንህን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የፀጥታ እና ሲቪል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በምርቃት ሥነሥርዓቱ ላይ ንግግር ያድረጉት የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስዬ ደጀን “ወደ ላቀ ኀላፊነት የተሰማራችሁ የፖሊስ አባላት እንኳን ደስ አላችሁ! ምን ጊዜም በላቀ የሥራ አፈጻጸም፣በላቀ ወታደራዊ ዲስፕሊን ሀገርና ሕዝባችሁን እንደምታገለግሉ እንተማመናለን” ብለዋል።

በምረቃ ሥነሥርዓቱ ላይ ሰልጣኞች ተገቢውን ስብዕናና ክህሎት እንዲጨብጡ ተደርጓል ተብሏል።

ዘጋቢ ፦ ጋሻው አደመ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበተለያዩ ክልሎች ለመከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ነው።
Next articleየሀገር ዋልታና መከታ የኾነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ስም ማጠልሸት መቆም እንዳለበት የሠራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች አስገነዘቡ።