
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሠላማዊ እና ሰማያዊ ውኃ የናኘበት የጣና ሐይቅ ጸጥታ ፍጹም የተለየ ስሜትን ይሰጣል፡፡ የውበት ሰገነት ለሆነችው የባሕር ዳር ከተማ ሌላ ገጸ ባሕሪ የሚያላብስ እና ከዓለማዊነት ወደ መንፈሳዊነት የሚያሸጋግር፤ ለንጽጽር የማይመች ድባብ በዚህ ሐይቅ ጥግ አለ፡፡ የአዕዋፋቱ ዝማሬ እና የዋኖሶቹ የኅብረት ትርኢት በባለሙያ የተቀመረ የሙዚቃ እና የመዝናኛ ዝግጅት ይመስላል፡፡
ገና በጠዋቱ በአንጋፋው የጣና ሐይቅ ትራንስፖር ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኝተናል፡፡ ተረጋግቶ ከተንጣለለው የጣና ሐይቅ ማዶ የሚመጣው ቀዝቃዛ እና ነፋሻማ አየር በሙቀቷ ለምትታማው የባሕር ዳር ከተማ ሌላ መልክ ሰጥቷታል፡፡ በትንሽ ሜትሮች ርቀት ሁለት የተለያዩ ክስተቶችን ለመታዘብ ባሕር ዳር ምቹ ሳትኾን አትቀርም፡፡ የከተማው ግርግር እና ወከባ ከጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ጀርባ ባለው የጣና ሐይቅ ግዛት ውስጥ ፈጽሞ አይስተዋልም፡፡ አርምሞ መለያው ነው፡፡
የባሕር ላይ ተጓዦች እንደ የብስ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ሁሉ በጠዋት ተገኝተው የጀልባዎችን እና የታንኳዎችን እንቅስቃሴ ይጠባበቃሉ፡፡ አንዳንዶቹ ቀድመው ገብተው ቦታ ቦታቸውን እንደያዙ ሰፊውን የጣና ሐይቅ አድማስ በአርምሞ ይከታተላሉ፡፡ ከእነዚህ ተጓዦች መካከል አብዛኞቹ መንፈሳዊ አባቶች እና የሀገሬው ሰዎች ናቸው፡፡ ደቅ እና ዘጌ ደግሞ ብዙ ተጓዦች ያሏቸው ደሴቶች ናቸው፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ ጎርጎራ ድረስ የሚዘልቅ የትራንስፖርት አገልግሎት ነበር አሉ፤ እሱ አሁን ላይ ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እና ለዓለማዊ ሕይዎት ወደ ደሴቶቹ ብዙ ተጓዦች በየሳምንቱ ይመላለሳሉ፡፡
የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የአንጋፋነቱን ያክል እድገቱ “እንደ ግመል ሽንት” ኾኗል የሚሉ ቢኖሩም ከጎርጎራ እስከ ናርጋ፤ ከደቅ እስከ ዘጌ ለመንፈሳዊ በረከት እና ዓለማዊ ሕይዎት የሚመላለሱትን ሁሉ አገልግሎት በመስጠት ተመስጋኝ ድርጅት ነው፡፡
የጣና ሐይቅ ህልውና እስካለ ድረስ አንድ ቀን ይህ ድርጅት የተሻለ ቁመና ይዞ የቀደመ ክብሩን እና ሥሙን ያድሳል ብለን እናስባለን፡፡
እኔ እና የሥራ ባልደረቦቼ ለሥራ ጉዳይ ወደ ደቅ ደሴት ለመጓዝ ጀልባ ውስጥ ገብተን ወጭ ወራጁን እየታዘብን ነው፡፡ ብዙዎቻችን ለአካባቢው እንግዳ ባንኾንም ከቆየንበት እና ከመጣንበት ድባብ የተለየው የጣና ሐይቅ ዙሪያ አርምሞ እኛም በፀጥታ እንድንታዘብ ሳያስገድደን አልቀረም፡፡ የመንቀሳቀሻ ተራችን ደርሶ የረጋውን ሐይቅ የምትረብሸው ጀልባችን ፊቷን ወደ ሰሜን አቅጣጫ አቅንታ ተፈተለከች፡፡ እንደ ድንኳን የተወጠረውን ውኃ እየከፈለች የምታንቦጫርቀው “ንጋት” በሐይቁ ውስጥ የሚኖሩትን ነፍሳት ሳይቀር የሚረብሽ ሳይኾን አይቀርም፡፡ “እንደ ሰው ልጅ ጥበበኛም፤ ጥጋበኛም ያለ አይመስልም” ለማለት ያስገድዳል፡፡
በርቀት ስናየው የነበረውን አድማስ እየተጠጋን ስንሄድ የመጣንበትን የከተማ ድባብ እየራቅነው ሄደናል፡፡ ባሕር ዳር ጣና ሐይቅ ላይ ኾነውም ሲመለከቷት ፍጹም ትስባለች፡፡ አሁን ጀልባችን የብስ የራቀው የጣና ሐይቅ ክፍል ውስጥ ነች፡፡ በሐይቁ መካከል ቁጥር ተሰጥቷቸው እንደ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት አልፎ አልፎ የተቀመጡ ብረቶችን እናያለን፤ አቅጣጫ ጠቋሚዎች ናቸው አሉን፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት እንደተቀመጡ የሚነገርላቸው እነዚህ አቅጣጫ ጠቋሚዎች የሐይቁን ጥልቀት እና የጀልባዎቹን መንገድ የሚያመላክቱ እንደኾኑ ነገሩን፡፡ ሐይቁን የሕይዎታቸው አንድ ክፍል ያደረጉት ብዙዎቹ የአካባቢው ነዋሪዎች በሐይቁ ዙሪያ ስላለው ነበር ሁሉ ከልምድ የተገኘ እውቀት አዳብረዋል፡፡
አሁን ከባሕር ዳር እየራቅን ወደ ሐይቁ ደሴቶች እየቀረብን መጥተናል፡፡ በርቀት የምንመለከታቸው የእንጦስ እና ክብራን ገብርኤል ገዳማት ለእንግዳ ተጓዥ ቀልብ የሚገዙ እና ቅድሚያ የሚታዩ ገዳማት ናቸው፡፡ እንደ ጡት መንታ ኾነው ግራ እና ቀኝ የበቀሉት እነኝህ ገዳማት በግምት ከ45 ደቂቃ የሐይቅ ላይ ጉዞ በኋላ በቅርብ እርቀት እየተመለከተናቸው አለፍን፡፡ ገዳማቱ የተሸፈኑበት እና የለበሱት አረንጓዴ ደን የተመልካችን ቀልብ ይስባል፡፡ መንትዮቹን ገዳማት በመካከላቸው ያለው ቀጭን የሐይቁ ክፍል ነጣጥሎ አስቀምጧቸዋል፡፡ ቀደም ባለው ዘመን ክብራን ገብርኤል የወንዶች፤ እንጦስ ገዳም ደግሞ የሴቶች ብቻ ገዳማት ነበሩ ይባላል፡፡ በእንጦስ የነበሩ ሴት መናንያን በተለያዩ ምክንያቶች በመሰደዳቸው አሁን ላይ ያ ታሪክ ያለ አይመስልም፡፡
ከብራንን እና እንጦስን አልፈን አሻጋሪ የዘጌ ደሴትን እና የአራራት ተራራን እያማተርን ወደ ሰሜን አቅጣጫ እየተጓዝን ነው፡፡ ገነት በምድር ናት፤ ያውም ደግሞ በኢትዮጵያ ለሚሉ ሰዎች ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት የአራራት ተራራ ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ አሁን ርእሱን በውል ከማላስታውሰው መጽሐፍ ላይ እንዳነበብኩ አስታውሳለሁ፡፡ አራራት በዚያ የሐይቁ አጼ ግዛት አሻጋሪ የከተመ ግዙፍ እና ባለ ግርማ ሞገስ ተራራ ነው፡፡ ውበቱን ለመናገር ከጸሃፊ ይልቅ ሰዓሊ መሆን ሳይሻል አይቀርም፡፡ ያንን ውበት ያዩ ከምድራዊ ሕይዎት ማለፍ በኋላ አለ በሚሉት ሌላ ሕይዎት አራራትን ቀጣይ መክተሚያ አድርገው መምረጣቸው አያስገርምም፡፡
የዘጌ ወደብን በቅርብ እርቀት እያስተዋልን ታክከነው ወደ ሰሜን አቅጣጫ እየተጓዝን ነው፡፡ ለተከታታይ ሁለት ሰዓታት የዘለቀውን ከዘጌ እስከ ናርጋ ሥላሴ አቅራቢያ ያለውን የሐይቅ ላይ ጉዞ መናገር አይቻልም፡፡ በርቀት ከሚታየው የብስ ውጭ ሙሉ በሙሉ በሐይቁ የተሸፈነ በመኾኑ በቅርብ እርቀት ስላለ ነገር የሚተረክ የለም፡፡ በዚያ የተንጣለለ ሐይቅ ላይ አልፎ አልፎ ውር ውር የሚሉት ዋኖሶች ብቻ ናቸው፡፡
አንድ ጊዜ ጀልባዋን እየቀደሙ ሌላ ጊዜ ከጀልባዋ በኋላ የሚመጡት ዋኖሶች ለረጂም ጊዜ በሐይቁ ውስጥ ሰጥመው የመቆየት የተለየ ተሰጥኦን አይተንባቸዋል፡፡ ጀልባዋ በምታልፍበት የውኃ ክፍል የሚረበሹት አሳዎች በእንቅስቃሴ ላይ ስለሚኾኑ አሳዎቹን ለመያዝ ስለሚመቻቸው ዋኖሶቹ የጀልባዋን እንቅስቃሴ ተከትሎ በአካባቢው አይጠፉም፡፡ “ዓሳን መብላት በብልሃት” የሚለው የሰው ልጅ ብሂል ለዋኖሶችም ይሰራል ማለት ነው፡፡
ከሦስት ሰዓታት ገደማ የሐይቅ ላይ ጉዞ በኋላ ደቅ ደሴት ላይ ደርሰናል፡፡ ከደቅ ደሴት በቅርብ ርቀት የሚገኘው የናርጋ ሥላሴ ገዳም እንደ እንጦስ እና ክብራን መንትያዎች ያመሳስላቸዋል፡፡ በጣና ሐይቅ ከሚገኙ ደሴቶች ሁሉ በስፋቱ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የደቅ ደሴት መንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን ዓለማዊ ሕይዎትም ይመራበታል፡፡ የሰባት ደብር ሀገር!
ሠላማዊ እና ሰማየዊ ውኃ የናኘበት የጣና ሐይቅ ፀጥታ ፍጹም የተለየ ስሜትን ይሰጣል፡፡ የውበት ሰገነት ለሆነችው የባሕር ዳር ከተማ ሌላ ገጸ ባሕሪ የሚያላብስ እና ከዓለማዊነት ወደ መንፈሳዊነት የሚያሸጋግር፤ ለንጽጽር የማይመች ድባብ በዚህ ሐይቅ ጥግ አለ፡፡ የአዕዋፍቱ ዝማሬ እና የዋኖሶቹ የሕብረት ትርኢት በባለሙያ የተቀመረ የሙዚቃ እና የመዝናኛ ዝግጅት ይመስላል፡፡
ገና በጠዋቱ በአንጋፋው የጣና ሐይቅ ትራንስፖር ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኝተናል፡፡ ተረጋግቶ ከተንጣለለው የጣና ሐይቅ ማዶ የሚመጣው ቀዝቃዛ እና ነፋሻማ አየር በሙቀቷ ለምትታማው የባሕር ዳር ከተማ ሌላ መልክ ሰጥቷታል፡፡ በትንሽ ሜትሮች ርቀት ሁለት የተሉያዩ ክስተቶችን ለመታዘብ ባሕር ዳር ምቹ ሳትሆን አትቀርም፡፡ የከተማው ግርግር እና ወከባ ከጣና ሐይቅ ትራንስፖርት ጀርባ ባለው የጣና ሐይቅ ግዛት ውስጥ ፈጽሞ አይስተዋልም፡፡ አርምሞ መለያው ነው፡፡
የባሕር ላይ ተጓዦች እንደ የብስ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ሁሉ በጠዋት ተገኝተው የጀልባዎችን እና የታንኳዎችን እንቅስቃሴ ይጠባበቃሉ፡፡ አንዳንዶቹ ቀድመው ገብተው ቦታ ቦታቸውን እንደያዙ ሰፊውን የጣና ሐይቅ አድማስ በአርምሞ ይከታተላሉ፡፡ ከእነዚህ ተጓዦች መካከል አብዛኞቹ መንፈሳዊ አባቶች እና የሀገሬው ሰዎች ናቸው፡፡ ደቅ እና ዘጌ ደግሞ ብዙ ተጓዦች ያሏቸው ደሴቶች ናቸው፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ ጎርጎራ ድረስ የሚዘልቅ የትራንስፖርት አገልግሎት ነበር አሉ፤ እሱ አሁን ላይ ስለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እና ለዓለማዊ ሕይዎት ወደ ደሴቶቹ ብዙ ተጓዦች በየሳምንቱ ይመላለሳሉ፡፡
የጣና ሐይቅ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የአንጋፋነቱን ያክል እድገቱ “እንደ ግመል ሽንት” ሆኗል የሚሉ ቢኖሩም ከጎርጎራ እስከ ናርጋ፤ ከደቅ እስከ ዘጌ ለመንፈሳዊ በረከት እና ዓለማዊ ሕይዎት የሚመላለሱትን ሁሉ አገልግሎት በመስጠት ተመስጋኝ ደርጅት ነው፡፡ የጣና ሐይቅ ህልውና እስካለ ድረስ አንድ ቀን ይህ ድርጅት የተሻለ ቁመና ይዞ የቀደመ ክብሩን እና ሥሙን ያድሳል ብለን እናስባለን፡፡
እኔ እና የሥራ ባልደረቦቸ ለሥራ ጉዳይ ወደ ደቅ ደሴት ለመጓዝ ጀልባ ውስጥ ገብተን ወጭ ወራጁን እየታዘብን ነው፡፡ ብዙዎቻችን ለአካባቢው እንግዳ ባንሆንም ከቆየንበት እና ከመጣንበት ደባብ የተለየው የጣና ሐይቅ ዙሪያ አርምሞ እኛም በፀጥታ እንድንታዘብ ሳያስገድደን አልቀረም፡፡ የመንቀሳቀሻ ተራችን ደርሶ የረጋውን ሐይቅ የምትረብሸው ጀልባችን ፊቷን ወደ ሰሜን አቅጣጫ አቅንታ ተፈተለከች፡፡ እንደ ድንኳን የተወጠረውን ውኃ እየከፈለች የምታንቦጫርቀው “ንጋት” በሐይቁ ውስጥ የሚኖሩትን ነፍሳት ሳይቀር የሚረብሽ ሳይሆን አይቀርም፡፡ “እንደ ሰው ልጅ ጥበበኛም፤ ጥጋበኛም ያለ አይመስልም” ለማለት ያስገድዳል፡፡
በርቀት ስናየው የነበረውን አድማስ እየተጠጋን ስንሄድ የመጣንበትን የከተማ ድባብ እየራቅነው ሄደናል፡፡ ባሕር ዳር ጣና ሐይቅ ላይ ሆነውም ሲመለከቷት ፍጹም ትስባለች፡፡ አሁን ጀልባችን የብስ የራቀው የጣና ሐይቅ ክፍል ውስጥ ነች፡፡ በሐይቁ መካከል ቁጥር ተሰጥቷቸው እንደ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት አልፎ አልፎ የተቀመጡ ብረቶችን እናያለን፤ አቅጣጫ ጠቋሚዎች ናቸው አሉን፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት እንደተቀመጡ የሚነገርላቸው እነዚህ አቅጣጫ ጠቋሚዎች የሐይቁን ጥልቀት እና የጀልባዎቹን መንገድ የሚያመላክቱ እንደሆኑ ነገሩን፡፡ ሐይቁን የሕይዎታቸው አንድ ክፍል ያደረጉት ብዙዎቹ የአካባቢው ነዋሪዎች በሐይቁ ዙሪያ ስላለው ነበር ሁሉ ከልምድ የተገኘ እውቀት አዳብረዋል፡፡
አሁን ከባሕር ዳር እየራቅን ወደ ሐይቁ ደሴቶች እየቀረብን መጥተናል፡፡ በርቀት የምንመለከታቸው የእንጦስ እና ክብራን ገብርኤል ገዳማት ለእንግዳ ተጓዥ ቀልብ የሚገዙ እና ቅድሚያ የሚታዩ ገዳማት ናቸው፡፡ እንደ ጡት መንታ ሆነው ግራ እና ቀኝ የበቀሉት እነኝህ ገዳማት በግምት ከ45 ደቂቃ የሐይቅ ላይ ጉዞ በኋላ በቅርብ እርቀት እየተመለከተናቸው አለፍን፡፡ ገዳማቱ የተሸፈኑበት እና የለበሱት አረንጓዴ ደን የተመልካችን ቀልብ ይስባል፡፡ መንትዮቹን ገዳማት በመካከላቸው ያለው ቀጭን የሐይቁ ክፍል ነጣጥሎ አስቀምጧቸዋል፡፡ ቀደም ባለው ዘመን ክብራን ገብርኤል የወንዶች፤ እንጦስ ገዳም ደግሞ የሴቶች ብቻ ገዳማት ነበሩ ይባላል፡፡ በእንጦስ የነበሩ ሴት መናንያን በተለያዩ ምክንያቶች በመሰደዳቸው አሁን ላይ ያ ታሪክ ያለ አይመስልም፡፡
ከብራንን እና እንጦስን አልፈን አሻጋሪ የዘጌ ደሴትን እና የአራራት ተራራን እየማተርን ወደ ሰሜን አቅጣጫ እየተጓዝን ነው፡፡ ገነት በምድር ናት፤ ያውም ደግሞ በኢትዮጵያ ለሚሉ ሰዎች ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት የአራራት ተራራ ነው፡፡ ይህንን ሃሳብ አሁን ርእሱን በውል ከማላስታውሰው መጽሃፍ ላይ እንዳነበብኩ አስታውሳሉ፡፡ አራራት በዚያ የሐይቁ አጼ ግዛት አሻጋሪ የከተመ ግዙፍ እና ባለ ግርማ ሞገስ ተራራ ነው፡፡ ውበቱን ለመናገር ከጸሃፊ ይልቅ ሰዓሊ መሆን ሳይሻል አይቀርም፡፡ ያንን ውበት ያዩ ከምድራዊ ሕይዎት ማለፍ በኋላ አለ በሚሉት ሌላ ሕይዎት አራራትን ቀጣይ መክተሚያ አድርገው መምረጣቸው አያስገርምም፡፡
የዘጌ ወደብን በቅርብ እርቀት እያስተዋልን ታክከነው ወደ ሰሜን አቅጣጫ እየተጓዝን ነው፡፡ ለተከታታይ ሁለት ሰዓታት የዘለቀውን ከዘጌ እስከ ናርጋ ሥላሴ አቅራቢያ ያለውን የሐይቅ ላይ ጉዞ መናገር አይቻልም፡፡ በርቀት ከሚታየው የብስ ውጭ ሙሉ በሙሉ በሐይቁ የተሸፈነ በመሆኑ በቅርብ እርቀት ስላለ ነገር የሚተረክ የለም፡፡ በዚያ የተንጣለለ ሐይቅ ላይ አልፎ አልፎ ውር ውር የሚሉት ዋኖሶች ብቻ ናቸው፡፡
አንድ ጊዜ ጀልባዋን እየቀደሙ ሌላ ጊዜ ከጀልባዋ በኋላ የሚመጡት ዋኖሶች ለረጂም ጊዜ በሐይቁ ውስጥ ሰጥመው የመቆየት የተለየ ተሰጥኦን አይተንባቸዋል፡፡ ጀልባዋ በምታልፍበት የውኃ ክፍል የሚረበሹት አሳዎች በእንቅስቃሴ ላይ ስለሚሆኑ አሳዎቹን ለመያዝ ስለሚመቻቸው ዋኖሶቹ የጀልባዋን እንቅስቃሴ ተከትሎ በአካባቢው አይጠፉም፡፡ “ዓሳን መብላት በብልሃት” የሚለው የሰው ልጅ ብሂል ለዋኖሶችም ይሰራል ማለት ነው፡፡
ከሦስት ሰዓታት ገደማ የሐይቅ ላይ ጉዞ በኋላ ደቅ ደሴት ላይ ደርሰናል፡፡ ከደቅ ደሴት በቅርብ ርቀት የሚገኘው የናርጋ ሥላሴ ገዳም እንደ እንጦስ እና ክብራን መንትያዎች ያመሳስላቸዋል፡፡ በጣና ሐይቅ ከሚገኙ ደሴቶች ሁሉ በስፋቱ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው የደቅ ደሴት መንፈሳዊ ብቻ ሳይኾን ዓለማዊ ሕይዎትም ይመራበታል፡፡ ከባሕር ዳር ከተማ 37 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የደቅ ደሴት ወደ ስምንት የሚደርሱ አድባራት እና ገዳማት ይገኙበታል፡፡ ከዳጋ እስጢፋኖስ እስከ ናርጋ ሥላሴ፣ ከሐይቅ ቅድስት አርሴማ እስከ እመቤታችን ኮታ ማርያም፣ ከዝባድ ኢየሱስ እስከ ጆጋ ዮሐንስ እና ከጋደና ጊዮርጊስ በቅርቡ እስከ ተገደመው ቤተ አዳም ድረስ በዚች ደሴት ስር ይገኛሉ፡፡ ደቅ ቀድሞ በነበሯት አድባራት ልክ “የሰባት ደብር ሀገር!” እየተባለችም ትጠራለች ብለውናል፡፡
ደቅ ቅድመ ነዋሪዎቿ መናንያን እና ገዳማዊያን የኾኑ መንፈሳዊያን ብቻ ነበሩ ይባላል፡፡ የኋላ ኋላ ግን ዓለማዊያንም ወደ ደሴቷ በመምጣት መኖር እንደጀመሩ ይነገራል፡፡ የፈለገ ሕይዎት ጣና ሐይቅ ቅድስት አርሴማ ደብር አሥተዳዳሪ ቀሲስ መንበረ አክሊሉ ዓለማዊያን ወደ ደሴቷ የመጡበት መንገድ አራት ዋና ዋና ምክንያቶች እንደነበሩት ይነገራል ይሉናል፡፡ የግራኝ ጦርነት፣ እቴጌ ምንትዋብ ናርጋ ሥላሴን በሚያሰሩበት ወቅት፣ በአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ ንግስና እና በድርቡሽ ጦርነት ወቅት የመጡ ናቸው ተብሎ ይታሰባል ብለውናል፡፡
በአራቱም አቅጣጫ ከየብስ ጋር የማትዋሰነው የደቅ ደሴት በውስጧ ሲገቡ በዙሪያዋ ያለውን ሐይቅ ታስረሳለች፡፡ እርፍ አገላብጦ የሚያርስ ገበሬ የሚኖርባት ደሴት ከበርበሬ እስከ ፍራፍሬ፤ ከባቄላ እስከ ቡና የማታመርተው የላትም፡፡ ደቅ ውስጥ እንኳን በመንፈሳዊ ሕይዎት በዓለማዊ ሕይዎትም መኖር የተለየ ሠላም አለው፡፡ ሀገሬዎቿ ሰው ወዳድ ናቸው፡፡ ማንጎ እንደ እሸት፤ እንደ ውኃ ወተት ለእንግዳ ይቀርባል፡፡ ትንሽ የቆየንባት ደቅ ብዙ አትርፈን ተመለስንባት፡፡ በቅርቡ የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ወደብ ሊያስገነባ ሥራው ተጀምሯል፡፡ ወደቡ ሲጠናቀቅ ደቅን ተመላልሰን እንጎበኛት ይኾናል፡፡ ወደ ባሕር ዳር ልንመለስ ነው…
በታዘብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!