የብልፅግና ፓርቲ 10 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው።

120

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መድረኩ የተጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ሕይዎታቸውን ላጡት ለፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባል ለአቶ ግርማ የሺጥላ የ1 ደቂቃ የኅሊና ፀሎት በማድረግ ነው።

በውይይቱ ላይ የሁሉም ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች የተገኙ ሲሆን ባለፉት 10 ወራት ብልፅግና ፓርቲ ከላይኛው እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ለመፈፀም ያቀዳቸው ተግባራት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ በመገምገም ላይ ነው።

በተጨማሪም እንደ ፓርቲ የተያዙ እቅዶች በበጀት ዓመቱ መግቢያ ላይ በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ተፈፃሚ ይሆኑ ዘንድ ግባቸውን ያልመቱ እቅዶችም በቀሪ ጊዜያት ሊጠናቀቁ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ ባለፉት 10 ወራት በሁሉም ዘርፎች ውስጥ የተሠሩ ሥራዎች አጠቃላይ ሪፖርት በገለፃ መልክ የቀረበ ሲሆን ለግምገማ ክፍት እንዲሆን ለተሳታፊዎች ቀርቧል።

በተለይም የፓርቲያችንን ሁለንተናዊ የፖለቲካ፣ የኮሙኒኬሽን፣ የአደረጃጀት ፓርቲያዊ አቅምን ሊያዳብሩ የሚችሉ ተግባራት ባለፉት 10 ወራት በምን ያህል ደረጃ በተሳካ ሁኔታ እንደተፈፀሙ የግምገማው ይዘት በጥልቅ የሚዳስሳቸው ይሆናል።

ከ10 ወራት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በተጨማሪም የመድረኩ ቀጣይ ትኩረት የ2016 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ምን እንደሚመስሉ መዳሰስ ሲሆን በፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለፃ እንደሚደረግ ይጠበቃል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም በሚመጣው ክረምት ኅብረተሰቡ እና መላው የብልፅግና ፓርቲ አባላት፣ አመራርና ደጋፊዎችን በማሳተፍ በሚሠሩ ሰፋፊ የንቅናቄ ሥራዎች ዙሪያ አቅጣጫ የሚቀመጥ ሲሆን በግብርና፣ በአረንጓዴ አሻራ እና በበጎ ፍቃድ ሥራዎች ላይ ያተኮሩ እንቅስቃሴዎች በምን መልኩ መፈፀም እንደሚገባቸው ምክክር እንደሚደረግ ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል ባለፉት 10 ወራት 30 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
Next articleበአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በክልሉ እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ።