
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 13/2012 ዓ.ም (አብመድ) ወጣቶች የጥፋት ኃይሎች አጀንዳ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ ወላጆች መምከር እንደሚገባቸውም አሳስበዋል፡፡
ኢትዮጵያ የምትታወቀው በኅብረ ብሔራዊነት እና አንድነት ዜጎች ተከባብረዉ የሚኖርባት ሀገር በመሆን እንደሆነ ነው ምሁራኑና የሀገር ሽማግሌዎቹ የገለጹት፡፡ ‹‹በዚህ ወቅት ያጋጠማት ፈተና ግን ከኢትዮጵያውያን እሴት ያፈነገጠ ነው›› ብለዋል የሁለቱ ክልሎች የሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን፡፡
ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን በማመላትም ሁሉም ስለሠላም ሊዘምርና ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ‹‹አንዱ ለሌላው ሰው በመሆኑ ብቻ ሊያስብለትና ሊቆረቆርለት ግድ ይለዋል፤ ወጣቱ በስሜትና አሉባልታ እየተነዳ ጥፋት ከመሥራት ሊቆጠብ ይገባል›› ሲሉም መክረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ -ከአዲስ አበባ