
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውና የጎንደር አብያተ-መንግስታት አካል የሆነው የጉዛራ ቤተ-መንግስት የጥገና ሥራ ተጀምሯል።
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኘው የጉዛራ ቤተ መንግስት የመፍረስ አደጋ ከተደቀነበት ረጅም ጊዜያትን አስቆጥሯል፡፡
ቤተ መንግስቱን ከመፍረስ አደጋ ለመታደግ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ጥናቶችን ሲያካሂድ መቆየቱ ተገልጿል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ) ፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ እና ሌሎችም የክልል እና የዞን አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለጥገና ሥራው የሚውል በጀት በፌደራል መንግስት በኩል 35 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የተመደበ ሲሆን በ1 አመት ከ6 ወር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!