“በኢትዮጵያና ቻይና ከፍተኛ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር ይገባል” አቶ ደመቀ መኮንን

74

ባሕር ዳር ፡ ግንቦት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያና ቻይና ከፍተኛ ተቋማት መካከል ጉድኝት መፍጠርና በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ፡፡

አቶ ደመቀ በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ መጽሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከቻይና የምርምር ተቋማት ጋር የዕውቀት ልውውጥ ማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ አለው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በቤጂንግ የውጭ ጥናቶች ዩኒቨርሲቲ መካከል ያለው የአማርኛ ቋንቋ ትብብር የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ያግዛልም ነው ያሉት።

የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ጂያ ዌንጂያን በበኩላቸው ቋንቋው በቻይና መሰጠቱ የኢትዮጵያን ባሕልና ታሪክ ለማስተዋወቅ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ሶስት የአማርኛ መመሪያ መጽሐፍት የተመረቁ ሲሆን ቻይናውያን የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ግጥም ማቅረባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር ተወያዩ።
Next articleበበጀት ዓመቱ 10 ወራት ለ 1 ሺህ 458 ድርጅቶች የታክስ ቅሬታ ውሳኔ ተሰጥቷል- የገቢዎች ሚኒስቴር