ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር ተወያዩ።

233

ባሕር ዳር: ግንቦት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር በቢሯቸው ተወያይተዋል። ርእሰ መሥተዳድሩ ዶክተር ይልቃል ከፋለ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እና ቻይና ረጅም ዘመናት የዘለቀ ጠንካራ የትብብር ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ።

በአማራ ክልልም በትምህርትና ሥልጠና፣ በቴክኖሎጂ ትውውቅና በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ ለመሥራት የጀመርነውን ግንኙነቶች ይበልጥ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። ክልላችን የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ የቻይና ባለሐብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩቱ የባሕር ዳር ከተማን የፋሽን ከተማ ለማድረግ እየሠራ መኾኑን ገለጸ።
Next article“በኢትዮጵያና ቻይና ከፍተኛ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር ይገባል” አቶ ደመቀ መኮንን