የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ኾነው እንዲፈቱ አመራሩ በአንድንት አስተሳሰብ መታገልና መሥራት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡

118

ወልድያ: ግንቦት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ ጋሻው አስማሜ የማንናትና ወሰን፣ የሕገ መንግሥት መሻሻል፣ በክልሉ ውጭ የሚኖሩ አማራዎች የውክልና ጥያቄ ፣ የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎችና ሌሎች መሰረታዊ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር መታገል ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህም መላ አመራሩ የጋራ አስተሳሰብ እና ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባ ነው አቶ ጋሻው በውይይቱ ያሳሰቡት ፡፡

በወይይቱ የተገኙት የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ ኢብራሂም ሙሀመድ (ዶ.ር) አማራ ከሌሎች ኢትዮጵያን የመገንባት ታሪኩን በሚመጥን ደረጃ የመፈጸም እና የመታገል አቅሙን ማሳደግ እንዳለበት ነው ያመለከቱት ፡፡

በየዘርፉ የእኔ ሃሳብ ብቻ ልክ ነው የሚል ሃሳብ ያላቸውን አካላት ወደ ጋራ ሃሳብ መግባባትና ተጠቃሚነት ለማምጣት የሀሳብ የበላይነት ወስዶ መሥራት እንዳለበት አቶ ኢብራሄም አመለክተዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር ሙሰጠፋ ውስጣዊ አንድነትን በማጎልበት የማኀበረሰቡን የሰላም፣ ልማትና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች መመለስ የሚችሉ መሪዎችን ለመፍጠር ኮንፈረንሱ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የዞኑና በዞኑ ሥር ያሉ የወረዳና የከተማ አሥተዳደር መሪዎች ”ፈተናዎችን በመቀየር ወደ ድል እናሻግር በሚል“ መሪ ሀሳብ በወቅታዊ ኹኔታዎችና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ እየመከሩ ነው።

ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየታላቁ ሕዳሴ ግድብን ከደለል ለመከላከል የፌደራል እና የክልሎችን መንግሥታት ቅንጅታዊ ሥራ እንደሚጠይቅ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡
Next article“የውስጥ አንድነትን በማጠናከርና በመደማመጥ የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መታገል ይገባል” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደሪ ወርቁ ኃይለማሪያም