የሰሜን ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከዞን፣ ከተማና ወረዳ የመንግሥት መሪዎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

73

ደባርቅ: ግንቦት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ውይይቱ “ፈተናዎችን ወደ እድል በመቀየር ሕዝባችን እናሻግራለን” በሚል መሪ ሐሳብ በወቅታዊ ሁኔታዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይመር ስዩም ኮንፈረንሱ በወቅታዊ ዞናዊ እና ክልላዊ ዞናዊ የፖለቲካና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች ላይ ተወያይቶ ወጥ አቋም ለመያዝና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለመገምገም ያለመ መሆኑን አንስተዋል።

አቶ ይመር ክልላዊና ዞናዊ ፈተናዎችን በድል ለመሻገር አመራሩ ጽንፈኝነት መታገል ይኖርበታል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ያለዓለም ፈንታሁን ጽንፈኝነት ብሔርና ዓለማ የለውም፤በተለያዩ ጊዜያቶች በመሪዎች ላይ የተፈጸሙ ግድያዎች የጽንፈኝነት ውጤቶች ናቸው፤ጽንፈኝነት ኹላችንንም የሚበላንና ሕዝብን መሪ አልባ የሚያደርግ መኾኑን ተገንዝበን በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ የማንነትና የወሰን ጉዳይ፤ ፍትሐዊ የመልማትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፤ፍትሐዊ የፖለቲካ ውክልና የማግኘትና መሰል ጥያቄዎችን ይዞ በመታገል ለውጥ ማምጣት መቻሉንም አውስተዋል።

መንግሥትም የሕዝብን ጥያቄዎች ለመመለስ ሠፊ ሥራ ሠርቶ ያመጣቸውን ተጨባጭ ለውጦች በቅጡ መረዳትና ያልተመለሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን በመገምገም ወጥ አቋም መያዝ ከኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
ከ 4 መቶ በላይ የዞን፣የከተማና የወረዳ መሪዎች የሚሳተፉበት ኮንፈረንሱ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚካሄድም ለማወቅ ተችሏል።

ዘጋቢ:-አድኖ ማርቆስ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከዞንና ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
Next articleበንጹሀን የባሕር ዳር ከነማ ደጋፊዎች ላይ የደረሠው ጥቃት መወገዝ የሚገባው የፀረ ሰላም እንቅስቃሴ መኾኑን ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ገለጹ።