ለኢትዮጵያ ውስብሰብ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሰረታዊ መፍትሔ ለማፍለቅ ያለመ ፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

68

አዲስ አበባ: ግንቦት 17/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ላጋጠማት ውስብሰብ ኢኮኖሚያዊ ችገሮች መሰረታዊ መፍትሔ ለማፍለቅ ያለመ ፓናል ውይይት
በፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ በገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች የፖሊሲ አማራጮችን በማዘጋጀት እና የመፍትሔ ሐሳቦችን በማመንጨት ለፖሊሲ አውጪዎች አጋዥ የሚኾን ሥራ እንዲሠሩ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ጠይቀዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያግዝ እና በሀገሪቱ አዲስ እይታ የሚያሰፍን ሥራ ለመሥራት ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤት ሚና የላቀ ድርሻ እንዳለው ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪዎች ከተለያዩ ምንጮች በሳይንስዊ መንገድ የተጠና እና የተነተኑ መረጃዎችን በማዘጋጀት ለትክክለኛ ውሳኔ የሚያበቃ መረጃ ማመንጨት እንደሚገባቸው ተገልጿል።

በውይይቱ የፖሊሲ አማራጮችን ለመመርመር እና የመፍትሔ ሐሳቦችን ለማመንጨት እንደሚያስችልም ዶክተር ፍጹም ገልጸዋል።

የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ከገለልተኛ ፖሊሲ አማካሪዎች የሚገኘውን በማስረጃ የተደገፈ እና ለመሰረታዊ ለውጥ የሚያግዝ መረጃዎችን መጠቀም እንደሚገባቸው በውይይቱ ተገልጿል።

ውስብስብ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት በተናጠል ሳይኾን በጋራ ጥረት እና ጉልበት መፍትሔ መስጠት እንደሚቻል የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ገልጸዋል።

የትኛውም መረጃ የተተነተነ እና ሀቀኝነቱ የተረጋገጠ ማድረግ ከተቻለ በኢትዮጵያ ለሚፈልገው ቀጣይነትም ያለው ለውጥ እና እድገት ማምጣት ይቻላል ብለዋል ገዥው።

ገለልተኛ የኢኮኖሚ አማካሪ ምክር ቤቱ ዛሬ በሚካሄደው ፎረም ሀገሪቱ ያለችበትን ኢኮኖሚያዊ ኹኔታ የተረዳ እና በቀጣይ በዘርፉ አወንታዊ ለውጥ ለማምጣት ልንጠቀምበት እንደሚገባ ተገልጿል።

ዘጋቢ:- ዳንኤል መላኩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ፤ ሕዝባችንን እናሻግር ” በሚል መሪ ሃሳብ በደሴ ከተማ የአመራሮች ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
Next articleየአፍሪካ ኅብረት ምስረታውን ሲያከብር ለአፍሪካውያን ሰላም፣ ደህንነት እና እድገትን ለማምጣት በመትጋት መኾን ይገባዋል ሲሉ የኅብረቱ ሊቀመንበር ገለጹ።