በኢትዮጵያ ትኩረት በሚሹ በሽታዎች ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየሠራ እንደሚገኝ ኢንድ ፈንድ የተሰኘ ግበረ ሰናይ ድርጅት ገለጸ፡፡

58

አዲስ አበባ ፡ ግንቦት 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ትኩረት በሚሹ በሽታዎች ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እየሠራ የሚገኘዉ ኢንድ ፈንድ ግበረ ሰናይ ድርጅት በኢትዮጵያ እያከናወነ ባላቸዉ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡ የኢንድ ፈንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ6 በሽታዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ የድርጅቱ የፕሮግራም ቴክኒካል ዳይሬክተር ኬብሮን ሀይሌ (ዶ.ር) ተናግረዋል፡፡ ቴክኒካል ዳይሬክተሯ በዓለም ደረጃ ወደ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ሰዎችን የሚያጠቃዉን የአንጀት ትላትል በሽታ በኢትዮጵያ ለመከላከል ተሠርቷል ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ከተጀመረበት 10 ዓመት ወዲህ ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸዉ በዋናነት የመድኃኒት ስርጭት ሥራዎች ተሰርቷልም ብለዋል፡፡

ከንጽህና አጠባበቅ ጋር ተያይዞ ችግሮች መኖራቸውን እና በዚህም ለበሽታ የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ መኾኑን ዶክተር ኬብሮን አስገንዝበዋል፡፡ ይህንን ለመከላከልም ሳኒቴሽን ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሠራ መቆየቱንም አንስተዋል፡፡የፕሮግራሙ ዳይሬክተር ካሮል ካሩቱ (ዶ.ር) ከስድስቱ በሽታዎች ውስጥ ትራኮማ አሁንም ትኩረት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ትራኮማን ለመከላከል ባከናወናቸዉ ተግባራት ውጤታማ እንደነበረም ጠቅሰዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዳያስፖራው ለገበታ ለትውልድ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።
Next article“እንዳለመታደል ኾኖ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያውያንም አያውቋትም” ፕሮፌሰር አደም ካሚል