“በአማራ ክልል የግብርና አስተራረስ ዘዴን ለማዘመን እየተሠራ ያለው ሥራ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው” አቶ ደመቀ መኮንን

135

ባሕር ዳር: ግንቦት 15/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ለብዙ ዓመታት ሲሰራበት የኖረው የግብርና አስተራረስ ዘዴን ለማዘመን እየተሰራ ያለው ስራ በክልሉ በምርትና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለጹ።

አቶ ደመቀ መኮንን በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ላይ የአማራ ክልል ይዞ የመጣውን ምርት ጎብኝተዋል።አቶ ደመቀ በጉብኝት ወቅት እንደተናገሩት፣ እንደ ሀገር ግብርናውን ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው፤ በዚህም ውጤት እየተመዘገበ ነው በማለት ተናግረዋል።እንዲሁም በአውደ ርዕዩ በአማራ ክልል እየተሰሩ ያሉ የግብርና ስራዎችን በስፋት ተመልክተናል ፤ ምን ደረጃ ላይ እንዳለም ለማየት ችለናል ብለዋል።

በዚህም ዝርያን ለማሻሻልና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር በሰብል ልማት፣ በእንስሳት ሀብትና መሰል ምርቶች የተመለከትነው ነገር የሚበረታታና ተስፋ ሰጭ ነው ብለዋል። በመሆኑም፣ በአሁኑ ወቅት በአማራ ክልል ለብዙ ዓመታት ሲሰራበት የኖረው የግብርና አስተራረስ ዘዴን ለማዘመን እየተሰራ ያለው ስራ በክልሉ በምርትና ምርታማነት ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። በአጠቃላይ፣ እንደሀገር በቀጣይ በግብርናው ዘርፍ መልካም ውጤቶች ይመዘገባሉ በማለት ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዓባይ ከግብጽ እስከ አረብ ሊግ!
Next articleዳያስፖራው ለገበታ ለትውልድ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።