
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ከቀናት በፊት የተወሰኑ ተማሪዎች ምግብ እንደተመረዘ በመናገራቸው አለመረጋጋት ተፈጥሮ ነበር፡፡
የዩኒቨርሲቲው፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ችግሩን ለመፍት ጥረት ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ በመጨረሻም በተማሪዎች መካከል እርቀ ሠላም በማውረድ ወደ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመግባት ስምምነት ላይ መደረሱ ታውቋል፡፡
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳድርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ባለው ባዬ (ዶክተር) ለአብመድ እንደተናገሩት ዛሬ ከሰዓት በኋላ በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ ፊት ለፊት በተማሪዎች መካከል እርቀ ሠላም እየተፈጸመ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- አብርሃም በዕውቀት