ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ3ኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መድረክ በይፋ ከፈቱ።

113

ባሕር ዳር ፡ ግንቦት 14/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ3ኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር መድረክ በይፋ ከፍተዋል።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ‘ክህሎት ለተወዳዳሪነት’ በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ አምስት ቀናት የሚቀጥል ነው።

በውድድሩ የፈጠራ ሥራዎች ዐውደ ርዕይ፣ፓናል ውይይትና ሌሎች መርኃ ግብሮች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ውድድሩ ብቃትና ክህሎት ያላቸው ወጣቶች መብቃታቸውን ለማሳየትና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ሁነኛ ሚና ይኖረዋል።

ኢትዮጵያን ለማበልፀግና ሁሉንም ዘርፍ ለማዘመን ፈጠራ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የግብዓት ችግር ባለመኖሩ ፈጠራና ክህሎትን ማሳደግ እንደሚገባ ነው ያመላከቱት።

የፈጠራ ባለሙያዎች በሚያጋጥሟቸው ተግዳሮቶች ሳይበገሩ ፈተናዎችን እንደመስፈንጠሪያ ተጠቅመው፤ ውጤት ተኮር ሥራዎች ላይ አበክረው እንዲሰሩም አሳስበዋል።

ዛሬ በቀረቡ የፈጠራ ሥራዎችም ትልቅ ተስፋ ሰጭ ፈጠራዎችን እንደተመለከቱ ገልፀው፣ ሚኒስቴሩ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ሥራዎች ማከናወኑን ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article62 በመቶ የክልሉ ወጣቶች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሳተፉ ተገለጸ፡፡
Next articleቺርቤዋ ጉንቤት 15 ጌርክ 2015 ምሬት አሜታ /አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን/