“በመስኖ ከለማው ስንዴ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ያህሉ ምርት ተሰብስቧል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

70

ባሕር ዳር: ግንቦት 13/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በ2015 ዓ.ም በበጋ መስኖ ከ213 ሺህ 232 ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል። ከዚህም 10 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል የስንዴ ምርት ለማምረት ታቅዷል፡፡ በሥራው ላይ ከአንድ ሚሊየን በላይ አርሶ አደሮች ተሳትፈውበታል፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የመስኖ ባለሙያ ተሻለ አይናለም በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

እስካሁን 159 ሺህ 697 ሄክታር መሬት የታጨደ ሲኾን 136 ሺህ 664 ሄክታር መሬት ተወቅቶ ወደ ጎተራ ገብቷል ብለዋል፡፡ ከዚህም 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት መሰብሰቡንም ጠቁመዋል፡፡

አቶ ተሻለ አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን በወቅቱ በመሠብሰብ በበልግ ዝናብ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ የሚያደርጉትን ርብርብ አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአቶ ማርቆስ ዘውዱ ለደብረታቦር ጠቅላላ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በለገሱት 10 ሚሊዮን ብር የተገነባ የድንገተኛ ህክምና መሥጫ ሕንጻ ተመረቀ።
Next article“ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች”