
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 12/2012 ዓ.ም (አብመድ) የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ሂደት ሕዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደተከናወነ ይታወቃል፡፡ በድምጽ መስጫው ቀን ማምሻ ላይ ቆጠራው ተጠናቅቆ የሕዝበ ውሳኔው ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡ ትናንት የሁሉም ምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ተጠናቅቀው ወደ 15 የማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤቶች ገብተዋል፤ ዛሬ ደግሞ የዞን ማስተባበሪያ ጣቢያ ላይ ውጤቱን የማጠቃለል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡
ቦርዱ ውጤት የሚያሳውቀው ነገ ቅዳሜ ሕዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትዕግስት እንዲጠብቁም ቦርዱ ጥሪ አቅርቧል፡፡