የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

102

ባሕርዳር: ግንቦት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት “ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” በሚል መሪ መልእክት በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል፡፡

አባላቶቹ ለሀገሪቱ የጀርባ አጥንት የኾነውን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን እና የአርሶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል የግብርና ሚኒስቴር እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚበረታቱ መኾናቸውን ገልፀዋል፡፡

አውደ ርዕዩ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቆይ ሲሆን በግብርናው መስክ የተሰማሩ ከ70 በላይ የምርምርና ፈጠራ ሥራዎች፣ ዲጅታላይዜሽን ፣ ግብርና እና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ መቅረባቸውን ፋናቢሲ ዘግቧል።

በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን አውደ ርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም መክፈታቸው ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከፊታችን ሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ ይሰጣል” ትምህርት ሚኒስቴር
Next article“ውስን የኾነውን የበጀት ሀብት ይበልጥ ጥቅም በሚሠጡ ተግባራት ላይ በማዋል የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል” የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ