
ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ግንቦት 10/2015 ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን አሳውቋል።
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ነው ያለው ሚኒስቴሩ።
ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!