ሕብረት ባንክ ከዘምዘም ባንክ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።

151

አዲስ አበባ ፡ ግንቦት 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ሕብረት ባንክ የቴክኖሎጂ፤ የዕውቀት ሽግግርና ልምድን ማካፈል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙርያ ከዘምዘም ባንክ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

በዚህ ስምምነት መሰረትም ሁለቱ ባንኮች በቴክኖሎጂ፣ በዕውቀት ሽግግር እና ስልጠና ዘርፎች አብረው የሚሰሩ ሲሆን ሕብረት ባንክም በዘርፉ ያለውን የካበተ ዕውቀትና ልምድ ያካፍላል። ዘምዘም ባንክም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ያለውን አቅም ስልጠናዎችን በመስጠት ያካፍላል ተብሏል ።

ዘጋቢ፦ ሳሙኤል ኪሮስ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማሪታይም አካዳሚ ለ21ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 119 መርከበኞች አስመረቀ፡፡
Next article“አባት ያሳመራት፣ ትውልድ የሚኮራባት”