
ባሕር ዳር: ግንቦት 09/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ልዑክ በ ’ላፕሴት’ ፕሮጀክት ስብስባ ላይ ለመሳተፍ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።
ልዑኩ ጁባ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማሃዲ አቀባበል አድርገውለታል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑክ በደቡብ ሱዳን በሚኖረው ቆይታ ኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳንን በትራንስፖርት ለማስተሳሰር ያለመው ላፕሴት ፕሮጀክት አስመልክቶ በተዘጋጀው ውይይት ላይ እንደሚሳተፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በተጨማሪም ከደቡብ ሱዳን የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽና የጋራ ፍላጎት በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
የላፕሴት ፕሮጀክት እ.አ.አ በ2012 በኢትዮጵያ፣ኬንያና ደቡብ ሱዳን ሀገራት መሪዎች የጋራ ስምምነት ወደ ሥራ እንዲገባ ውሳኔ መተላለፉ የሚታወስ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!