የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን የግብርና ኤግዚቢሽን ጎበኙ ።

53

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን የግብርና ኤግዚቢሽንን መጎብኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በጉብኝቱ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉን (ዶ.ር) ጨምሮ የፌደራል፣ የክልሎች እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የሚዲያ ተቋማት አመራሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተው ለሕዝብ እይታ ክፍት የሆነውን የግብርና አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ካባለፈው ሳምንት ጀምሮ በግብርና ሚኒስቴር አዘጋጅነት በተሰናዳው አውደ ርዕይ ላይ ተገኝተው በግብርናው ዘርፍ የተገኙ ስኬቶችን የሚያሳዩ ሥራዎች በመጎብኘት ላይ ናቸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአዲስ አበባ ከተማ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች  በከተማ ግብርና እየተሳተፉ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleየኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መደበኛ ባልኾነ መንገድ መሻሻል መጀመሩን የሰላም ሚኒስቴር ገለጸ።