“ኢትዮጵያን እንገንባ“ በሚል ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን አውደ ርዕይ ከግንቦት 10 ጀምሮ ሊካሄድ ነው።

37

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) አውደ ርዕዩን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከዲ ኤም ጂ ዓለም አቀፍ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ጋር በጋራ በመተባበር የሚያዘጋጁት መኾኑ ተገልጿል፡፡

የዲ ኤም ጂ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ሲኒየር ምክትል ፕሬዚደንት ቢን ግሪኒሽ እንዳሉት በተለያዩ ሀገራት ሁነቶችን የማዘጋጀት ልምዳቸውን ተጠቅመው የተሳካ ሁነት ለማሰናዳት መዘጋጀታቸውን ጠቁመው፤ እንደ ጣሊያን ፣ህንድ፣ ቻይናና ቱርክ መሠል ሀገራት ይሳተፋሉ ብለዋል።

በዚህም ለሀገሪቱ በተለይ አዲስ አበባን ከግማሽ ሚሊየን ዶላር በላይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ዝግጅት ይኾናል ብለዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ እንዳስታወቁት ከግንቦት 10 እስከ 12 ቀን 2015 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

በአውደ ርዕዩ ከ26 ሀገራት የተውጣጡ 116 ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ኩባንያዎች እና ከ6 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በአውደ ርዕዩ በቴክኖሎጂ ሽግግር ሌሎች ሀገራት እንዴት እንዳለፉ ልምድ ይቀሰምበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዘጋቢ፦ ድልነሳ መንግስቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዓለም ባንክ የ58 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው” የሸዋሮቢት ከተማ አሥተዳደር
Next articleበአዲስ አበባ ከተማ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች  በከተማ ግብርና እየተሳተፉ መኾኑ ተገለጸ።