“የማዕድን ሃብታችንን በአግባቡ በማልማት የሀገራችንን ኢኮኖሚ እንገነባለን” የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ

56

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን በባሕርዳር ከተማ እየገመገመ ነው። የቢሮው ኀላፊ አቶ ኃይሌ አበበ “የማዕድን ሃብታችንን በአግባቡ በማልማት የሀገራችንን ኢኮኖሚ እንገነባለን” ሲሉ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል እምቅ የማዕድን ሃብት እንደሚገኝ የጠቀሱት ቢሮ ኀላፊው ይህንን ሃብት በመጠን፣ በዓይነት እና በክምችት በመለየት ጥቅም ላይ ለማዋል ቢሮው እየተንቀሳቀሰ ነው ብለዋል። በማዕድን ሃብት ልማት ሥራ ላይ የሚከናወኑ ተግባራትን ጥንካሬ እና ድክመት በመገምገም ዘርፉ ሁነኛ የሥራ እንድል መፍጠሪያና የኢኮኖሚ መሠረት እንዲኾን በትኩረት እየተሠራ ስለመኾኑም አቶ ኃይሌ ተናግረዋል።

የክልሉ ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ “ማዕድን አዲሱ የንጋት ተስፋ ለክልላችን” የሚል መሪ ሃሳብ በመያዝ በአማራ ክልል ውስጥ ያሉ የማዕድን ሃብቶችን የመለየት እና የማጥናት ሥራ በትኩረት እያከናወነ እንደሚገኝ ቢሮ ኀላፊው ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጣና ሐይቅ የዓሣ ምርት እንዲጨምር ሕገደንቦችን መተግበር እንደሚገባ የአማራ ክልል እንሥሣትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽሕፈት ቤት አሳሰበ፡፡
Next article“በዓለም ባንክ የ58 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተሠሩ ነው” የሸዋሮቢት ከተማ አሥተዳደር