በአዲስ አበባ ከተማ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች  በከተማ ግብርና እየተሳተፉ መኾኑ ተገለጸ።

52

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ በሳይንስ ሙዚየም  እየተካሄደ ያለው  የከተማ ግብርና ኤግዚቢሽን በአመራሮች ተጎብኝቷ።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ  ሽጉጤ የከተማ ግብርና በአዲስ አበባ ከተማ አይቻልም ተብሎ የነበረ ቢኾንም  አሁን ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸውን የኀብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ያደረገ ነው ብለዋል። ብዙዎቹን ተጠቃሚ ያደረገው ይሄው ዘርፍ በዚህ ዘጠኝ ወር ለ15 ሺህ ወገኖች የሥራ እድል መፈጠሩንም  ተናግረዋል።

አቶ ባዩ  ሽጉጤ እንዳሉት ይህ የከተማ ግብርና ኤግዚቢሽን የገበያ ትስስር ከመፍጠር አኳያ ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል።

ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ማዕከል አድርገን እየሠራን እንገኛለን ያሉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ  የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ አስኪያጅ  ጥራቱ በየነ፤ በአዲስ አበባ ከተማ  የከተማ ግብርና ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ይገኛል ብለዋል።

ይህ የከተማ ግብርና የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ ሁነኛ መፍትሔና መልስ የሚስጥ ስለመኾኑም  ተናግረዋል።

በከተማዋ ከ300 ሺህ በላይ ነዋሪዎች  በከተማ ግብርና እየተሳተፉ እንደሚገኙ ገልጸዋለ።

የኢፌዴሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ግርማ አመንቴ  ግብርናችን ከገጠር ወደ ከተማ እየተሸጋገረ ያለና በዘመናዊ መልኩ እየተሠራበት የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እያደረገ የሚገኝ ዘርፍ ነው ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ሳሙኤል ኪሮስ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያን እንገንባ“ በሚል ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን አውደ ርዕይ ከግንቦት 10 ጀምሮ ሊካሄድ ነው።
Next articleየሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን የግብርና ኤግዚቢሽን ጎበኙ ።