አንድ ነጥብ አምስት ቢልዮን ብር ያስመዘገቡ 126 ኢንተርፕራይዞች ወደ መካከለኛ ባለሐብትነት ተሸጋገሩ።

69

ባሕር ዳር:ግንቦት 06/2015 ዓ.ም (አሚኮ) “ክህሎት ለተወዳዳሪነት” በሚል መሪ መልዕክት ለ8ኛ ጊዜ የሚካሄደው ክልል አቀፍ የቴክኖሎጂ ፣ የክህሎት፣ የጥናት እና ምርምር ውድድር ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ ተጀምሯል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የከተማ አሥተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት የደብረ ብርሃን ከተማ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባሳየችው ዕድገት በከተማዋ በአሁኑ ላይ ከሰባት መቶ በላይ ኢንዱስትሪዎች ይገኛሉ ብለዋል።

በከተማዋ ካሉት ኢንዱስትሪዎች ውስጥም ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች የተሰማሩ ናቸው ብለዋል ሲል የዘገበው ደብረ ብርሃን ከተማ ኮምዩኒኬሽን ነው።

የሥራና ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ አቶ አረጋ ከበደ በበኩላቸው ኢንተርፕራይዞቹ በተለያዩ መስኮች ተሰማርተው ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል አስመዝግበዋል ብለዋል።

ሥራና ሥልጠና ቢሮው ወደ ባለሐብትነት የተሸጋገሩትን ኢንተርፕራይዞች ለክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨትመንት ቢሮ አስረክቧል። የተሸጋገሩት ኢንተርፕራይዞች የቦታና የብድር አቅርቦት እንደሚመቻችላቸውም ጠይቀዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ዴኤታ ንጉሱ ጥላሁን ፥ ኢንተርፕራይዞችን ማሸጋገር ብቻ በቂ አይደለም ብለዋል፡፡ የመሥሪያ ቦታ ፣ ካፒታል ማሟላት እና ለአምራቾቹ የገበያ ትሥሥር መፍጠር ከመንግሥት የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የውበት ሠገነት፣ ተወዳጅ እመቤት”
Next articleበአማራ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ዘጠኝ ድልድዮችን በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየሠራ መኾኑን የክልሉ መንገድ ቢሮ ገለጸ።