“ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ምሳሌ የሚኾን ተቋም ነው” አቶ ቢያዝን እንኳኾነ

66

ባሕር ዳር:ግንቦት 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዮ በዓሉን በባሕር ዳር ከተማ ሲያከብር በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢያዝን እንኳኾነ ባስተላለፉት መልዕክት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ትውልድ ከሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደብ እና ለማኅበረሠብ ለውጥ እየተጋ ያለ ዩኒቨርሲቲ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለባሕር ዳር ከተማ ድምቀት ለሀገርም ኩራት ሲሆን ከዚህ ባሻገርም ዩኒቨርሲቲው የሰላም ተቋም መኾኑን በተግባር ያረጋገጠ እንደኾነም ገልጸዋል።

አቶ ቢያዝን ዩኒቨርሲቲው ግቢውን ውብ አድርጎ በመሥራት ምሳሌ መኾን የቻለ ስለመኾኑም ተናግረዋል። ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው
ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ምሳሌ የሚኾን ተቋም ነው ያሉት ቢሮ ኃላፊው የጥበብ ጓዳ ነውም ብለውታል።

ዩኒቨርሲቲው ከአጋር አካላት ጋር መሥራት ያውቅበታል የሚሉት አቶ ቢያዝን ለተለማቸው የለውጥ ሥራዎች ሁሉም አካላት እገዛ እንዲያደርጉ እና ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብረው እንዲሠሩ ጠይቀዋል። ቢሯቸውም ለዩኒቨርሲቲው ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።

አቶ ቢያዝን “ዩኒቨርሲቲያችን የዕውቀታችን ምንጭ መኾኑን አረጋግጠናል” ነው ያሉት።

ዘጋቢ፦ምሥጋናው ብርሃኔ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር በቱሪዝሙ ዘርፍ ተመራጭ እንድትኾን የማይተካ ሚና እየተጫወተ ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)
Next article“ተማሪ ከታተረ፣ መምህርም ከተጋ ጥሩ ውጤት እውን ይሆናል” መምህር ይበልጣል አዝዘው