“ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር በቱሪዝሙ ዘርፍ ተመራጭ እንድትኾን የማይተካ ሚና እየተጫወተ ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)

155

ባሕር ዳር:ግንቦት 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዮ በዓል በባሕርዳር ሲከበር በበዓሉ ላይ የተገኑት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው ባሕርዳርን በማሳደግ በኩል እየተጫወተ ያለው ሚና ትልቅ እንደኾነ ነው የገለጹት።

ባሕርዳር የትምህርት ከተማ እንድትኾን ባለፉት 60 ዓመታት የበኩሉን እየተወጣ ስለመምጣቱም ነው ያብራሩት።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተማዋ ላይ በተለይም ሹምአቦ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የሕዝብ ቤተ መጽሐፍት በመገንባትም የራሱን አሻራ እያሳረፈ ያለ የከተማዋ አለኝታ ተቋም ስለመኾኑም ነው የተናገሩት።

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በከተማዋ የመንገድ ልማት ዘርፍም ትልቅ እገዛ እያደረገ ያለ ዩኒቨርሲቲ እንደኾነም ነው ከንቲባው ያረጋገጡት።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የከተማዋን ፕላን አሻሽሎ ሠርቶ በማቅረብም ያደረገው አስተዋጽዖ በቀላሉ እንደማይታይም አመልክተዋል።

ዘጋቢ፦ ምሥጋናው ብርሃኔ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 60 ዓመታት የሚሠሩ እጆችን ያፈራ ተቋም እንደኾነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፍሬው ተገኝ(ዶ.ር) ገለጹ።
Next article“ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ምሳሌ የሚኾን ተቋም ነው” አቶ ቢያዝን እንኳኾነ