ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 60 ዓመታት የሚሠሩ እጆችን ያፈራ ተቋም እንደኾነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፍሬው ተገኝ(ዶ.ር) ገለጹ።

71

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 60 ዓመታት የሚሠሩ እጆችን ያፈራ ተቋም እንደኾነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፍሬው ተገኝ(ዶ.ር) ገለጹ።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የ60ኛ ዓመት በዓሉን በባሕር ዳር እያከበረ ነው።

በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርሲቲውን ጉዞ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፍሬው ተገኝ (ዶ.ር) እንዳሉት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፖሊ ቴክኒክ ጀምሮ እስከ ግዙፍ የትምሕርት ክፍሎችን ከፍቶ የሚሠሩ እጆችን ያፈራ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲ መኾኑን ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው በባሕር ዳር አካባቢ ትምህርት እንዲስፋፋ ግዙፍ ቤተ መጽሐፍት መገንባቱንም ነው ያስረዱት።

ዶክተር ፍሬው እንዳሉት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምሥራቅ አፍሪካ የመጀመሪያው የኾነውን የቴክስታይል የትምህርት ዘርፍ ማቋቋም የቻለም ስለመኾኑ አስገንዝበዋል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት ከትምህርት ዘርፍ በተጨማሪ በማኀበረሰብ አቀፍ ሥራ ላይ በመሳተፍ ኅብረተሰቡን እያገለገለ ስለመኾኑም ነው ያስገነዘቡት።

ዘጋቢ፦ ምሥጋናው ብርሃኔ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በቦሩ ሜዳ ሆስፒታል በተደረገልን ነጻ የዓይን ቀዶ ሕክምና የዐይን ብርሃናችን በመመለሱ ተደስተናል” ታካሚዎች
Next article“ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባሕር ዳር በቱሪዝሙ ዘርፍ ተመራጭ እንድትኾን የማይተካ ሚና እየተጫወተ ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)